1 ሳሙኤል 9:16-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. “ነገ በዚህ ጊዜ ከብንያም ምድር አንድ ሰው ወደ አንተ እልካለሁ፤ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪ እንዲሆን ቅባው፤ እርሱም ሕዝቤን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ይታደጋል። እነሆ፤ ሕዝቤን ከላይ ተመልክቻለሁ፤ ጩኸቱ ከእኔ ዘንድ ደርሶአልና።”

17. ሳሙኤል ሳኦልን ባየው ጊዜ እግዚአብሔር፣ “ያ የነገርሁህ ሰው እነሆ፤ እርሱም ሕዝቤን ይገዛል” አለው።

18. ሳኦልም በቅጥሩ በር ላይ ወደ ሳሙኤል ቀረብ ብሎ፣ “የባለ ራእዩ ቤት የት እንደሆነ ትነግረኛለህ?” ሲል ጠየቀው።

1 ሳሙኤል 9